log

☦WELCOME TO☦

Debre Tsehay Kidist Selassie EOTC of Calgary

Rooted in the ancient Orthodox Christian faith,
we welcome all to worship God, grow in Christ,
and experience the beauty of the Orthodox tradition.

kidest slase hero
OUR ORTHODOX FAITH
whatsapp image 2026 08 06 at 01.21.4944

“እኛ ግን ለጸሎትና ቃሉን ለማገልገል እንተጋለን።” — የሐዋ. ሥራ 6፥4

 

የአስተዳዳሪው መልእክት

 

ቅዱሳን ሐዋርያት እንዳስተማሩን፣ የማኅበረ ካህናትና የምዕመናን የጋራ አገልግሎት ለእግዚአብሔር መንግሥት ዕድገት መሠረት ነው። ቤተ ክርስቲያናችንም በስብከተ ወንጌል፣ በጸሎት፣ በመንፈሳዊና በማኅበራዊ አገልግሎት ምዕመናንን በማገልገልና ተተኪ ትውልድን በማፍራት ላይ ትገኛለች።

በእግዚአብሔር ቸርነትና በምዕመናን ትብብር፣ የጀመርናቸውን መንፈሳዊና የልማት ሥራዎች በማጠናከር ለቀጣዩ ትውልድ ዘላቂ መንፈሳዊ ቅርስ ለማስረከብ እንተጋለን።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር። አሜን!

 

መልአከ ፀሐይ ቀሲስ ፋሲካ እምቅድመዓለም

 

“But we will give ourselves continually to prayer and to the ministry of the word.” — Acts 6:4

 

Administrator’s Message

 

Following the example of the Holy Apostles, our church recognizes the shared responsibility of the clergy and faithful in serving the Kingdom of God. Through prayer, the ministry of the Gospel, spiritual growth, and community service, we strive to strengthen our congregation and nurture future generations in the Orthodox faith.

By the grace of God and through the dedication of our faithful, we continue to strengthen our spiritual and community ministries and work toward leaving a lasting legacy of faith for generations to come.

Glory be to God. Amen!

 

Melake Tsehay Qesis Fasika Emqidme Alem

whatsapp image 2026 08 06 at 01.21.4944

“እኛ ግን ለጸሎትና ቃሉን ለማገልገል እንተጋለን።”   የሐዋ. ሥራ 6፥4

የአስተዳዳሪው መልእክት

ቅዱሳን ሐዋርያት እንዳስተማሩን፣ የማኅበረ ካህናትና የምዕመናን የጋራ አገልግሎት ለእግዚአብሔር መንግሥት ዕድገት መሠረት ነው።

holy trinity cathedral
አጋዕዝተ ዓለም ቅድስት ሥላሴ

አጋእዝተ ዓለም ሥላሴ በኃጢአት የተገነባውን የሰናዖር ግንብ ያፈረሱበት አንድነታቸውንና ሦስትነታቸውን በግልጽ ያሳዩበት ጥር ሰባት ቀን የከበረ በዓል እንደመሆኑ በቤተ ክርስቲያናችን በድምቀት ይከበራል፡፡ታሪኩ በኦሪት ዘፍጥረት ላይ እንደተጻፈ እንዲህ ይነበባል፡፡

አጋእዝተ ዓለም ሥላሴ በኃጢአት የተገነባውን የሰናዖር ግንብ ያፈረሱበት አንድነታቸውንና ሦስትነታቸውን በግልጽ ያሳዩበት ጥር ሰባት ቀን የከበረ በዓል እንደመሆኑ በቤተ ክርስቲያናችን በድምቀት ይከበራል፡፡ታሪኩ በኦሪት ዘፍጥረት ላይ እንደተጻፈ እንዲህ ይነበባል፡፡

የኖኅ የትውልድ ነገዶች ከምሥራቅም ተነሥተው በሄዱ ጊዜ በሰናዖር ምድር አንድ ሜዳ አገኙ፤ በዚያም ተቀመጡ።እግዚአብሔርም የአዳም ልጆች የሠሩትን ከተማና ግንብ ለማየት ወረደ።እግዚአብሔርም አለ።‹‹ኑ፥ እንውረድ፤ አንዱ የአንዱን ነገር እንዳይሰማው ቋንቋቸውን በዚያ እንደባልቀው።››እግዚአብሔርም ከዚያ በምድር ሁሉ ላይ በተናቸው፤ከተማይቱንም መሥራት ተው።ስለዚህም ስምዋ ባቢሎን ተባለ።እግዚአብሔር በዚያ የምድርን ቋንቋ ሁሉ ደባልቋልና፤ ከዚያም እግዚአብሔር በምድር ሁሉ ላይ እነርሱን በትኖአቸዋል። (ዘፍ.፲፩፥፩-፱)

አጋእዝተ ዓለም ሥላሴ አንድነታቸውን ሲያጠይቅ ‹‹ኑ እንውረድ›› ባሉት መሠረት ሥላሴ በስም በአካል በግብር ሦስት መሆናቸው እንረዳለን፤ የስም ሦስትነታቸው አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ነው፤ የግብር ሦስትነታቸውስ ደግሞ አብ ወላዲ ወልድ ተወላዲ መንፈስ ቅዱስ ሰራጺ የመሆኑ ምሥጢር ነው፤ የአካል ሦስትነታቸው ለአብ ፍጹም አካል ፍጹም ገጽ ፍጹም መልክ ስላላቸው ነው፤ ለወልድም ፍጹም አካል ፍጹም ገጽ ፍጹም መልክ አለው፤ ለመንፈስ ቅዱስም ፍጹም አካል ፍጹም ገጽ ፍጹም መልክ አለው፤ ለመሆኑ የሥላሴ ገጽ አካል ፊት እንደ ሰው ነውን? የሚል ጥይቄ የተነሣ እንደሆነ መልሱ‹‹አዎ፤ እንደ ሰው ነው›› ይሆናል፤ ነገር ግን የሰው ውሱን ጠባብ ፈራሽና በስባሽ ነው፤ የሥላሴ ግን እንዲህ አይደለም፤ በሰማይና በምድር፣ በአየርና በእመቅ የመላ ረቂቅ ሕያው ባሕርይ ነው፡፡‹‹ሰማይ ዙፋኔ ነው፤ ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤የምትሠሩልኝ ቤት ምን ዓይነት ነው? የማርፍበትስ ስፍራ ምንድን ነው? ይህ ሁሉ የእጄ ሥራ ነው፤ ይህም ሁሉ የእኔ ነው››እንዲል፤ (ኢሳ.፹፮፥፩-፪) የሥላሴ አንድነታቸው በመለኮት፣ በፈቃድ፣ በሥልጣን፣ ወዘተ በመሳሰሉት ነው

ሰማዕቱ ቅዱስ ቂርቆስ
ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ቅድስት ኢየሉጣ

የሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስንና የእናቱ ቅድስት ኢየሉጣን ታሪ

የሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስንና የእናቱ ቅድስት ኢየሉጣን ታሪክ ፡፡ በሦስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን በሮም ግዛት ክርስትና ቢስፋፋም በዚያው በጣዖት አምልኮ የተያዙ ብዙዎች ነበሩ፤ ይህም ለዘመኑ ክርስቲያኖች ፈታኝ ነበር፡፡ ይገርማችኋል ልጆች! ማንኛውም ክርስቲያን መሠረታዊ ፍላጎቶቹ እንዲሟሉለት ከፈለገ በጣዖት የሚያመልኩ ሰዎቸ ላቆሟቸው ጣዖቶች መንበርከክ (መስገድ) ግዴታው ነበር፡፡ ሰብአዊ መብቱን ከመገፈፉ ባሻገር ‹‹ተበድያለው›› ብሎ ወደ ፍርድ ቤት ሄዶ መብቱን የማስከበር ፍትሕ የማግኘት ዕድል አልነበረውም፡፡ በዚያ ላይ ደግሞ በየጊዜው ለክርስቲያኖች ፈታኝ የሆኑ አዋጆች ይወጣሉ፤ የክርስትናን ጎዳና ይበልጥ የሚያጠቡ ሕጎችም ዕለት ዕለት ይደነገጉ (ይወሰኑ) ነበር፡፡ ስለዚህም በወቅቱ የነበረ አንድ ክርስቲያን ሃይማኖቱን ከወደደ ይከሰሳል፤ እስከ መሰደድም ይደርሳል፡፡

ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! በዚህ አስጨናቂ ዘመን እግዚአብሔርን የሚያመልኩ በክርስትና ሃይማኖት የጸኑ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስ እና ቅድስት ኢየሉጣ የተባሉ ክርስቲያኖች ነበሩ፤ የዚህ ዘመን (የዘመነ ሰማዕታት) መልካም ፍሬዎች ናቸው፡፡ በዚህ በሮም ግዛት እለእስክድሮስ የተባለ ጨካኝ በጣዖት የሚያመልክ ንጉሥ ነበር፤ እናም ክርስቲያኖችን ጣዖት እንዲያመልኩ ያስገድዳቸው ጀመር፤ በዚህም የተነሣ ብዙዎች ጣዖትን ላለማምለክ ሀገር ጥለው ተሰደዱ፡፡ቅድስት ኢየሉጣም ባሏ በሕይወት ባለመኖሩ ከሕፃን ልጇ ቅዱስ ቂርቆስ ጋር ትኖር ነበር፡፡ ልጇ ቅዱስ ቂርቆስም ምንም እንኳን ገና ሦስት ዓመቱ ቢሆንም ነገረ ሃይማኖትንና ፍቅረ ክርስቶስን ታስተምረው ነበር፡፡ እለ ስክድሮስ ለጣዖት እንዲሰግዱ የክሕደት አዋጅን ሲያውጅ ቅድስቲቱ ለሕፃን ልጇ ራርታ ሽሽትን መረጠች፡፡ ሀብት ንብረቷን፣ ወገንና ርስቷንም ትታ ሕፃን ልጇን ተሸክማ ተሰደደች፡፡ መከራው ግን በሄደችበት አልተዋትም፡፡ እለስክንድሮስ ተከትሎ ባለችበት ቦታ አገኛት፡፡ ወታደሮች ልጇን ሳያገኙ እርሷን ብቻ ይዘው ወደ መኮንኑ አቀረቧት መኮንኑ፤ ‹‹ስምሽን ንገሪኝ›› ሲላት ‹‹ስሜ ክርስቲያን ነው›› አለችው፡፡ ‹‹ትክክለኛ ስምሽን ተናገሪ›› ቢላት ‹‹እውነተኛ ስሜ ክርስቲያን ነው፤ የዓለም መጠሪያ ስሜን ከፈለግህ ‹‹ኢየሉጣ ይባላል›› አለችው፡፡ እለእስክድሮስ የተባለ ጨካኝ በጣዖት የሚያመልክ ንጉሥ ‹‹ለጣዖት ልትሰግጂ ይገባል›› ባላት ጊዜ ‹‹እውነትን ይነግረን ዘንድ የሦስት ዓመት ሕፃን ልጄን ፈልገህ አምጣና ተረዳ›› አለችው፡፡ ንጉሡም ወታደሮቹን ፈልገው እንዲያመጡት ላካቸው፤ የሀገሩ ሰዎችም ልጆቻቸውን ስለ ደበቁ የተገኘው ቅዱስ ቂርቆስ ነበር፡፡

ውድ የእግዚአብሔር ልጆች! ቅዱሱ ሕፃን በወታደሮች ተይዞ ሲቀርብ መልኩ ያበራ ነበርና መኮንኑ ‹‹ደስ የተሰኘህ ሕፃን እንዴት ነህ›› አለው፤ ቂርቆስም መልሶ ‹‹ትክክል ነህ! እኔ በጌታዬ ክርስቶስ ዘንድ ደስታ ይጠብቀኛል፡፡ አንተ ግን ወደ ገሃነም ትወርዳለህ›› በማለት ተናገረ፡፡ በሕፃኑ ድፍረት የደነገጠው መኮንኑ በብስጭት ‹‹እሺ ስምህን ንገረኝ›› ብሎ ጠየቀው፤ ያን ጊዜም ‹‹ከንጹሕ ምንጭ የተቀዳ ስሜ ክርስቲያን ነው፡፡ እናቴ የሰየመችኝ ግን ቂርቆስ ብላ ነው›› ሲል መለሰለት፡፡ ከዚያም እየደጋገመ ‹‹እኔ ክርስቲያን ነኝ›› ብሎ በመመሥከሩ መኮንኑ ቅዱስ ሕፃን ቂርቆስና እናቱ ቅድስት ኢየሉጣን እንዲያሠቃዪቸው ወታደሮቹን አዘዘ፡፡

ልጆች! ከዚህ በኋላ በእነርሱ ላይ የተፈጸመባቸው ግፍ እና የደረሰባቸው መከራ እጅግ አስከፊና የሚዘገንን ነው:: መኮንኑ በትልቅ በርሜል ውኃ አስፈልቶ ከዚያም ውስጥ ኬሚካል በውስጡ ጨመረ፤ በዚህን ጊዜ ቅድስት ኢየሉጣ የልጇን ነገር አስባ በውስጧ ፍርሃት አደረ፤ ሆኖም ግን በዚህን ጊዜ ሕፃን ቂርቆስ በእምነቱ ጽኑ ስለነበር በመከራው ብዛት አልፈራም፡፡ ይገርማችኋል እንዲያውም የእናቱን ጭንቀትና ለእርሱ ስትፈራ ሲመለከት ‹‹እናቴ ሆይ ከብረቱ ጋን ትልቅነት የተነሣ አትፍሪ! ድንጋጤም አይደርብሽ! አናንያን፣ አዛርያንና ሚሳኤልን ከእቶን እሳት ያዳነ እኛንም ያድነናል፤ ሶስናን ከኃጢአተኞች እጅ ያዳናት፣ ዳንኤልን ከአንበሳ ጉድጓድ ያወጣ እኛንም ያድነናል›› አላት፤ ወደ እግዚአብሔርም ጸለየ፤ የዚያን ጊዜ እናቱ ተጽናናች፤ በረታችም፤ ፍርሃት ተወገደላት፤ ስለ እምነታቸው መስክረው ከፈላው የብረት ጋን ውስጥ ጨመሯቸው፤ በዚህን ጊዜ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ ወረደና በብረቱ ጋን የፈላውን ውኃ እንደ ውርጭ ውኃ አቀዘቀዘው፤ ኬሚካል ተጨምሮበት ሰውነታቸውን እንዲበጣጥሰው የተዘጋጀውን አቀዝቅዞ ውኃ አደረገው፤ ከመከራም አዳናቸው፡፡ እናቱም ለልጇ ‹‹እኔ የወለድኩህ እናትህ ነኝ፤ አንተ ደግሞ በእምነት ጽናትህ በመንግሥተ ሰማያት አባት ሆንከኝ›› አለችው፤ እግዚአብሔርንም አመሰገኑ፤

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ብዙ ቃል ኪዳን ገባላቸው፤ ‹‹እኔን መከተል የሚወድ ራሱን ይናቅ፤ መስቀሌንም ተሸክሞ ይከተለኝ›› ያለውን አማናዊ ቃል ሰምተው ለሙሽራው ለክርስቶስ ፍቅር ራሳቸውን አሳልፈው ሰጡ፡፡ (ማቴ.፲፮፥፳፬) ስለዚህ እኛም አምላክን ያከበሩ ቅዱሳንን እናከብራቸዋለን፤ ፈለጋቸውን እንከተላለን፡፡

ጻድቁ አቡነ ሀብተማርያም
አቡነ ሀብተ ማርያም

በተከበረች በኅዳር ፳፮ ቀን ንዑድ ክቡር ንጹሕ መነኰስ ኢትዮጵያዊ ጻድቅ አባታችን አቡነ ሀብተ ማርያም የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው።

በተከበረች በኅዳር ፳፮ ቀን ንዑድ ክቡር ንጹሕ መነኰስ ኢትዮጵያዊ ጻድቅ አባታችን አቡነ ሀብተ ማርያም የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው። ይህም ቅዱስ አባት የትውልድ ሀገሩ የራውዕይ በምትባል በስተ ምሥራቅ ባለች ሀገር ውስጥ ሲሆን በዚያም ስሙ ፍሬ ቡሩክ የሚባል አንድ ደግ ሰው ነበረ። ይህም ከክቡራን ሰዎች ወገን የሆነ ሰው እጅግ ሀብታምም የነበረ ሲሆን በሕጋዊ ጋብቻ ያጋቡት ቡርክት የሆነች ስሟ ዮስቴና የምትባል ሚስት ነበረችው። እርሷም በበጎ ምግባርና ሥራ የተጌጠች ናት። ይህችውም ደግ እናታችን በሕግ ተወስና ሳለች በጽኑዕ ገድል፣ በጾም በጸሎት በምጽዋትና በስገድትም ትጋደል ነበር።

በኋላም ጌታችን ስለ መንኖ ዓለምና መንኖ ይሪት የተናገረውን አስባ ለምናኔ ሀብቷን ሁሉንም ነገር ጥላ በቅርብ ወዳለ በረኃ ሄደች። በዚያም ወደሚገኝ አንድ ዋሻ ብትገባ ድንገት አንድ ደግ ባሕታዊን አገኘች። ያም ባሕታዊ ስለ አመጣጧ በተግሣጽ መልክ ቢጠይቃት እርሷ የመጣችው በዚያ ሰው እንደ ሌለ አስባ እንደሆነ ነገረችውና ከዚያ ወጥታ ወደ ሌላ ዋሻ ልትሄድ ስትል በመንፈስ ቅዱስ ተገልጦለት ከእርሷ ደግ የሆነ ቅዱስ ፍሬ እንደሚወጣ ነግሮ ወደ ዓለም እንድትመለስ አዘዛት። እርሷም “እግዚአብሔር የወደደው ይሁን” ብላ እያመሰገነች ተመልሳ ሳለ ከጥቂት ጊዜያት በኋላ ይህን ታላቅ ጻድቅ ፀንሳ ወለደች። በዚህም ሁላቸውም እጅግ ተሰኙ። እንደ ሥርዓቱም ሲጠመቅ የመጽሐፍ ስሙን “ሀብተ ማርያም” አሉት። እርሱ በሕግ በሥርዓት እያደገ ሄደ። ወደ ቤተ ክርስቲያንም ሲወስዱት “እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ” የሚለውን ጸሎት ቢሰማ እጅጉን ወደዳት። እርሷንም ይዞ ከቤቱ ሌሊቱን የሚጸልይና የሚጋደል ሆነ።

በኋላም አባቱ እረኝነት ሰዶት ሳለ በዚያ በጎቹን ሲጠብቅ ሳለ የበግ ጠባቂዎቹን “ዛሬ ዝናም ይዘንማልና እንግባ” አላቸው። እነርሱም “ምን ደመና አለና ነው፤ ቀኑ ብራ ነው” አሉት። ባልሰሙትም ጊዜ እርሱ በጎቹን ይዞ ወደ ቤቱ እንደገባ ኃይለኛ ዝናም፣ ነፋስና መብረቅ የቀላቀለ ዘነመ። በሌላም ጊዜ እንዲሁ አንድ እረኛ በጉልበት በአባ ሀብተ ማርያምን በትሩን ነጠቀው። “መልስልኝ” ብሎ በስመ እግዚአብሔር ቢያምለውም እምቢ አለው። ኋላም በተወው ጊዜ እግዚአብሔር ያን እረኛ በአየር ላይ ሠቅሎ አዋለው። እረኞቹም አባ ሀብተ ማርያምን በለመኑት ጊዜ እግዚአብሔር ነውና ስለ ስሙ ብሎ የቀጣው መሐሪው እርሱ ከወደደ ይማረው ሲል ያ እረኛ ተፈታና ወረደ። መጥቶም ከአባታችን እግር ወደቀ፡፡

ከብዙ ዘመናት በኋላም ስሟ እለ አድባር ወደምትባል ገዳም ገብቶ ከአባ መልከ ጼዴቅ እጅ መነኰሰ። ታላቅ ተጋድሎንም ይጋደል ጀመር። በባሕር መካከልም በመቆም መዝሙረ ዳዊትን ይደግምና ግንባሩም የባሕሩን አሸዋ እስኪነካ አምስት መቶ ጊዜ ይሰግዳል። እህልም መቅመስን ትቶ ልክ እንደ ዋልያዎች የዱር ቅጠል የሚመገብ ሆነ። ዐርባ ዐርባ፣ ሰማንያ ሰማንያ ቀንም የሚያከፍል ሆነ። በሌሊትም ቁሞ በማደር (በትጋሃ ሌሊት) በቀንም አራቱን ወንጌላት ዘወትር ይጸልያል። ይህን ጽኑዕ ተጋድሎውንም ያየ አምላካችን ተገለጠለት። አባ ሀብተ ማርያምም ከግርማው የተነሣ ደንግጦ በግንባሩ ተደፋ። ጌታችንም እፍ ብሉ አጽናንቶ ኃይል ጽንዕ ሰጥቶ አሥነሳውና ‹‹ወዳጄ ሀብተ ማርያም ላጠፋህ ሳይሆን ኃይል ጽንዕ ቃል ኪዳንም ልሰጥህ ነውና የመጣሁት አትፍራ›› አለው።

ጽኑዕ ተጋድሎው በሰማያት ስለ መጻፉ፣ የቅዱስ ማቴዎስንና የማርቆስን ወንጌል በሚያነብ ጊዜ ከሌሎች ሥውራን አበው ጋር የሚገናኝበትን የብርሃን ሠረገላ እንደ ሰጠው፣ የቅዱስ ሉቃስንና የቅዱስ ዮሐንስን ወንጌል በሚያነብ ጊዜ ደግሞ ሥጋውን ደሙን ለመቀበል ወደ ኢየሩሳሌም የሚሄድበትን የእሳት ሠረገላ እንደ ሰጠው ቃል ኪዳን ገባለት። ሰባት እጅግ የሚያስደንቁ አክሊላትንም አቀዳጀው። አንዱ ስለ ድንግልናው፣ ሁለተኛው ዓለምንና በውስጡ ያለውን ስለ መመነኑ፣ ሦስተኛው ፍጹም ስለ ሆነው ምንኲስናው፣ አራተኛው አራቱን ወንጌላት አዘውትሮ በማንበቡ፣ አምስተኛው ስለፍቅሩ ሲል ረኃብና ጥምን በመታገሡ፣ ስድስተኛው በልቡ ቂምንና በቀልን ባለማኖሩ፣ ሰባተኛው ደግሞ ስለ ንጹሕ የክህነት አገልግሎቱና በንጽሕና ስለሚያሣርገው መሥዋዕቱ መሆኑን ነገረው። መታሰቢያውን ለሚያደርጉና በስሙ ለሚዘክሩ፣ ከእነርሱ ጋር የሚኖርበትን አምስት መቶ የወርቅ አምዶስ ያሏትን ቦታ ሰጠሁህ አለው። ቅዱሳን መላእክትም ሁላቸው እየተደሰቱ ‹‹ወንድማችን ወደማያልቀው ሰማያዊ ደስታ ልንወስድህ መጥተናል››  አሉት።

ይህንንም በተናገረ ጊዜ ጌታችን በሦስትነቱ ተገልጦ ታየው። ‹‹መታሰቢያህን ለሚያደርግ፣ በስምህ ለቤተ ክርስቲያን መባ ለሚሰጥ፣ ወደዚህች አገር አገባዋለሁ። አራቱን ወንጌልም እያነበብህ ስለኖርህ የየአንዲቱን ቃል ፍሬዋን አንዳንድ ሺህ አደረግሁልህ። ይኸውም ከአንተ በኋላ ለሚመጡት ልጆችን መጽሐፈ ገድልህን ለሚያነቡና በእምነት ለሚሰሙ፣ የገድልህን መጽሐፍ በተነበበበት ውኃ ለሚረጩ፣ ለሚነከሩበት ይህ ቃል ኪዳን ሰጥቼሃለሁ።›› ከዚህም በኋላ ጌታችን ሦስት ጊዜ ሳመው። ነፍሱም ከሥጋው በሰላም ተለየች። ቅዱሳን መላእክትም በታላቅ ደስታ እያመሰገኑ አሣረጓት።

እግዚአብሔር አምላካችን በዚህ ታላቅ ጻድቅ ጸሎት ይማረን፤ በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር፤ ለዘለዓለሙ አሜን።

Worship & Service Times

Weekly Worship Schedule

Saturday Divine Liturgy

☦ Saturday Divine Liturgy
5:00 AM – 9:30 PM

 Bible Study
Wednesday • 5:00 PM

──────────────────

📍 Address
Calgary, Alberta

☎ (403) xxx-xxxx

Everyone is welcome to join our worship services

PHOTO GALLERY
whatsapp image 2026 08 06 at 01.21.4933
whatsapp image 2026 08 06 at 01.21.031
commites
whatsapp image 2026 08 06 at 01.21.032
whatsapp image 2026 08 06 at 01.21.4977
whatsapp image 2026 08 06 at 01.21.4955
whatsapp image 2026 08 06 at 01.21.4988
whatsapp image 2026 08 06 at 01.21.49887

📍Calgary Holy Trinity
    Ethiopian Orthodox
   Tewahedo Church

2712 37 Ave NE
Calgary, AB T1Y 5L3

📞

(403) XXX-XXXX (or leave hidden until available)

📧

eotc.holytrinityca@gmail.com

CONNECT WITH US

© 2026 Calgary Holy Trinity Ethiopian Orthodox Tewahedo Church.All Rights Reserved.